Other Sales

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በሰንቀሌ (አምቦ) መደበኛና ሙያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአገልግሎት ውጪ የሆኑትን ብረታብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በሰንቀሌ (አምቦ) መደበኛና ሙያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአገልግሎት ውጪ የሆኑትን ብረታብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ አዳማ የጨረታውን ሰነድ በመግዛት ጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ጨረታው ላይ ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-

1. የጨረታ ሰነድ የተዘጋጀው በኦሮሚኛ ቋንቋ ስለሆነ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ሊዩ ሊዩ ገቢዎች በሚለው ስም A/C ቁጥር 1000133792817 ላይ በማስገባት የጨረታ ሰነዱን በኮሌጅ ቅጥር ጊቢ ፋይናንስ ቢሮ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ማንኛውም ተጫራች ለውድድር ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) 10% ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. የሚሸጡ ብረታብረቶች አስመልክቶ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ3፡00 ጀምሮ እስከ 10፡30 በአካል በሰንቀሌ (አምቦ) መደበኛና ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በመሄድ ማየት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ጠዋት እስከ 4፡00 ሰዓት ተሽጦ የጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡45 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በይፋ በኮሌጁ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡

6. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

7. አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር 09-11-90-95-86 እና 09-13-01-50-46

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-21
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-21 10:45
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡45 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Oromia Police College
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 11, 2026)
  • Posted at: 2026-10-12T11:01:20.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders