Other Sales

ኦርቢስ የንግድ እና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ. የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገለ ተሽከርካሪ እና መለዋወጫዎች በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

አንጋፋ የአውቶሞቲቭ ኩባንያ ኦርቢስ የንግድ እና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ በኢትዮጵያ ስመጥር የሆኑትን የመርሰዲስ ቤንዝ እና ሬኖልት ተሸከርካሪዎች ብቸኛ አስመጪ መሆኑ ይታወቃል።

በመሆኑም ኩባንያችን በመጋዘናችን የቆዩ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን (የመርሰዲስ፣ የቦሽ፣ የሬኖልት፡ ቦማግ) እና የኮሚኒዩኬሽን መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች (የሞቶሮላ) እንዲሁም መርሰዲስ ቤንዝ፣ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራች የሆናችሁ ሜክሲኮ በሚገኘው መ/ቤታችን ዘወትር በሥራ ሰዓት በመገኘት የመኪኖቹን እና የመለዋወጫዎቹን ዓይነት እና ዝርዝር ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች ንብረቶቹን ከጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 02፡00-10፡30 ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ዝቅ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ 1 ውስጥ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።

2. ጨረታው አርብ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ተዘግቶ በማግስቱ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋት 04:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

3. ለጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይቻላል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።

5. በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ

6. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

7. ለበለጠ መረጃ መለዋወጫዎችን በተመለከተ፡ በስልክ ቁጥር፡ 0913 773 127 እንዲሁም ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 0974 656 420 ደውለው መረዳት ይችላሉ::

ኦርቢስ ንግድና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ

ስልክ፡ 115 516 211 / 115 510 078


Tender details

  • Deadline: 2026-10-15
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid opening: 2026-10-16 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Orbis Trading & Technical Center S.C
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Reporter (Oct 11, 2026)
  • Posted at: 2026-10-12T12:32:16.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders