Disposal Sale

አዋሽ ባንክ አ.ማ. ሲጠቀምባቸው የነበሩትን የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉን ብረቶች የጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ባንክ አ.ማ. ሲጠቀምባቸው የነበሩትን 21 ተሸከርካሪዎች እና 2 ሞተር ሣይክሎች በሎት (1) እና በሎት (2) (ጄኔሬተር” ዴስክቶፕ ኮምፒውተር “ፕሪንተር” ራክማውንት'' ቼክ ስካነር” ስካነር” ሰርቨር'' ዲሊንክ'' የወረፋ መጠበቂያ “የብር መቁጠሪያ'' የሣንቲም መቁጠሪያ'' መፈተሻ'' የሂሣብ መደመሪያ “የዶላር መፈተሻ ማሽን “ፋክስ' ፎቶ ኮፒ “የውሃ ማጣሪያ” ቴሌቭዥን'' ላሚኔቲንግ (ዱዋል ID ፕሪንተር)'' የሙቀት መለኪያ” ቬንትሌተር' ብሎ ወር'' ቴፕ ሪከርደር” ዩቪ የብር መፈተሻ ማሽን'' ኤክስቼንጅሬት ዲስፕሌይ ቦርድ'' አየር ማቀዝቀዣ'' ካሽ ቦክስ' ሪፍሪ ጂኔሬተር'' እሳት ማጥፊያ'' የተለያዩ ወንበሮች “ሶፋ'' የተለያዩ የማስታወቂያ ምልክቶች “የተለያዩ ጠረጴዛዎች'' የኮት መሰቀያ'' የመጽሐፍ መደርደሪያ'' ካዝና ፋይሊንግ ካቢኔት እና ላተራል ፋይሊንግ ካቢኔት) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

1. ስለጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መረጃ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-101 በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፣

2. ተጫራቾች በሎት 1 ላይ ለተገለጹት ተሸከርካሪዎች በባንኩ የተቀመጠውን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣

3. በሎት 2 ላይ ለተዘረዘሩት የቢሮ መገልገያ ንብረቶች ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ንብረት ያቀረቡትን ዋጋ ¼ ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣

4, ያለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣

5. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15%፣ ለተሸከርካሪዎቹ የስም ማዘዋወሪያ፣ የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት፣ በጨረታ ዋጋ እና የመንገድ ትራንስፖርት ባለሞያ ግምት መካከል ሊፈጠር የሚችለውን የተ.እ.ታ. የዋጋ ልዩነት ገዥ ይሸፍናል፣

6. ንብረቶቹን አሸዋ ሜዳ በሚገኙት የባንኩ መጋዘኖች እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹን በተመለከተ ልደታ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ በአካል ቀርበው እና የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመያዝ በወጣው ፕሮግራም መሠረት መጐብኘት ይቻላል፣

7. ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-11 ውስጥ ይከፈታል፣ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፣

8. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ¼ ኛ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ጨረታው ይሰረዛል፣

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ስለጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት በስልክ ቁጥር 0115-303 026 / 0115-303 014 / 0115-576 815/ ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

አዋሽ ባንክ አ.ማ. 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-20 10:10
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Awash Bank Share Company
  • Bid bond: 25% ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
  • Posted at: 2026-10-13T07:26:19.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders