Other Sales

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ እስፔርፓርት፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የግልፅ እና የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ እስፔርፓርት የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ስቃዎች በቀን 10/02/2019 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ፦

  1. በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ በዘርፍ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ በመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. ለሀራጅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤
  3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን በመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5 0/0) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  4. ለሀራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ ለራሱ ያቀርባል፣
  5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፤
  6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
  7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  8. በጨረታው ያሳሽነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
  9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
  10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሲሰጣቸው ይችላል፤
  11. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሽኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፤ 
  12. ተጫራቾች የሞሉትን ግልጽ ጨረታ ሰነድ ከቀን 10/02/2019 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በቀን 12/02/2019 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
  13. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው በቀን 12/02/2019 ከረፋዱ 4:15 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

N.B፦ አሽናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-22 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Somali
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T08:04:33.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders