Other Sales
የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ የብረት ተረፈ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች ወይም ለሌላ ግልጋሎት ሊያገለግሉ የሚችሉትን የብረታ ብረት ተረፈ-ምርቶችን በግመት 350(ሶስት መቶ ሃምሳ) ቶን የሚሆን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ፋብሪካችን የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ የብረት ተረፈ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች ወይም ለሌላ ግልጋሎት ሊያገለግሉ የሚችሉትን የብረታ ብረት ተረፈ-ምርቶችን በግመት 350(ሶስት መቶ ሃምሳ) ቶን የሚሆን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች/ ግለሰቦች ማስረጃቸውን በመያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኩባንያው ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትሹ ተወዳዳሪዎች አንዱን ኪሎግራም የብረት ተረፈ ምርት የምትገዙበትን ዋጋ በመግለጽ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ) ሲፒኦ ጋር በታሸገ ኤንቬሎፕ ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ብትወደድ ባህሩ ህንጻ 3ኛ ወለል በሚገኘው የኩባንያው ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።
የጨረታው አሸናፊ ድርጅት/ግለሰብ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የራሳቸውን ትራንስፖርት በማቅረብ ተረፈ-ብረቶቹን ማንሳት ይጠበቅባቸዋል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የገዙትን ጥሬ ዕቃ የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያችን ገቢ ሆኖ ኩባንያው ሌላ ጨረታ በማውጣት የሚሸጥ መሆኑን ያስታውቃል።
ኩባንያው ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፣ 251 552 2681 / 251 552 2731
አዲስ አበባ
የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-10-23
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-10-23 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Steel Pipe Mill P.L.C.
- Bid bond: 300,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
- Posted at: 2026-10-16T09:05:48.000Z