Other Sales
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Other SalesSales, Disposals and ForeclosureDisposal Sale
Addis Ababa
More tags
Aluminium ProductsSteel, Metals and AluminiumSteel Raw Materials and ProductsOther MetalsWood and Wood WorkingSpare Parts and Car Decoration MaterialsPlastic Raw MaterialsPlastic Raw Materials and ProductsPlastic ProductsKitchen EquipmentMetal and Metal WorkingBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksAmharic2merkatoELFORA Agro Industries P.L.C.
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
|
ያገለገሉ ዕቃዎች ዝርዝር |
ዕቃው የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ሲ ፒ አ (ብር) |
|
ቁርጥራጭ ብረቶች ፤ቁርጥራጭ ቆርቆርዎች፤ ቁርጥራጭ እንጨቶች የተለያዩ ጎማዎች ፤የእንጨት ፓሌቶች፤የግርግዳ ፓናሎች፤ ጣውላዎች የተለያዩ የመኪና ባትሪዎች፤ የውሀ ሮቶ ፤አሮጌ በርሜል እና አሮጌ ድስቶች ወ.ዘ.ተ |
ሎት 1 ኤልፎራ ዋናው መ/ቤት (አዲስ አበባ) ሎት 2.ኤልፎራ መልጌ እርሻ እና አግሮ ፕሮሰሲንግ -(መልጌ ወንዶ) ሎት 3.ኤልፎራ ሻሎ እርሻ ልማት(ሀዋሳ ሻሎ) |
200,000.00 (ዋና መ/ቤት) 200,000.00 (መልጌ ወንዶ) 200,000.00 (ሀዋሳ ሻሎ)
|
- ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ አሴት ታክስ (VAT) ወይም ተርን ኦቨርታክስ (TOT) የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አዲስ አበባ ላይ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ጉርድ ሾላ (ላምበረት) አካባቢ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት መግዛት ይችላሉ፤ የጨረታ ሰነዱ መግዣ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ) ነው።
- ተጫራቾች ዋጋ ከመስጠታቸው በፊት ዕቃዎች በሚገኙበት ከተማ በአካል በመገኘት ማየት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከ9/02/2019ዓ/ም – 20/02/2019ዓ/ም ድረስ ላሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለጨረታ ማሰከበሪያ /Bid bond/ የሚሆን ብር ከላይ የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በእያንዳንዱ ሎት በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለበት።
- ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ ይደረጋል።
- ጨረታው በእለቱ በ20/02/2019 ዓ/ም ከቀኑ 7፡30 ታሽጎ በእለቱ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኤልፎራ ዋና መ/ቤት 4ተኛ ፎቅ ግብይት ዲፓርትመንት ይከፈታል።
- ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-09 54 49 53 63 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-10-30
- Bid closing time: 13:30
- Bid opening: 2026-10-30 14:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ELFORA Agro Industries P.L.C.
- Bid bond: 200,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T09:34:33.000Z
- Source: Qelal Tenders