Spare Parts and Car Decoration Materials

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችና ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 15/2019

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሐራጅ ጨረታ እንዲሁም . የተለያዩ ንብረቶችን (የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውብት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ተሽከርካሪዎችን እና ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et  ላይ በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በመሆኑም

1. በዕቃ ግልፅ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ፎቶ በማንሳት(ስካን በማድረግ) ኦንላይን የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et ማያያዝ ይኖርበታል።

2. በተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.PO) ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

3. በጨረታው ላይ የዕቃው ወይም የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።

4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

5. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE አሰርተው ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦከሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

6. የተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ብር 200,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት። ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ

7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

 

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

 

የጨረታው አይነት

 

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ኢ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

የዕቃ ግልፅ

 

እስከ 17/02/2019

 

18/02/2019 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡ዐዐ ሰዓት ይከፈታል።

2

የተሸከርካሪ ሐራጅ

እስከ 18/02/2019

 

እስከ 19/02/2019 (ከ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ኦንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ደቂቃ) መሠረት ይካሄዳል።

 

8. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- ሙሉ በሙሉ የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et  (በኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ።

9. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።

11. ከላይ በተ/ቁ 0 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመስከተ መረጃ ስማግኘት፦ በስልክ ቁጥር 09-05-11-55-11

አድራሻ፡- ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከስላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301(ኦክሽን ኢትዮጵያ)

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ፡- 011-470-8503

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀስበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ስፌት ያስው ህንጻ

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ / ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-29 10:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T14:20:21.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders