Other Sales

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶች መሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡-AAU/NCB/pdi/10/2019/26
ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶች ሽያጭ ጨረታ

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከላይ በሎት የተጠቀሱትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

2. እቃዎቹ የሚገኙበት አድራሻ 6 ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንብረት አስተዳደር ክፍል ሲሆን ለመግዛት ፍላጎትና ብቃት ያላቸው ተጫራቾች በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል፡፡

3. ጨረታው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ሥነ-ሥርዓት መሰረት ይፈፀማል::

4. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ሀ/ በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግና ደረሰኙን ይዘዉ በመቅረብ ስለእቃዎቹ ሙሉ ዝርዝር የያዘዉን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸዉ አድራሻ እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይተዉ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸዉም፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 7 (ሐ) በተጠቀሰዉ አድራሻ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸዉ አድራሻ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ወይም በፊት በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ከጨረታ መዝጊያ ጊዜ በፊት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ተጋባዥ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በዩኒቨርሲቲው ስም አሰርተዉ አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች ከዉድድሩ ከወጣ የተያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል፡፡

7.

  • ሀ/ ሰነዶቹ የሚሸጡበት አድራሻ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 307
  • ለ/ የጨረታዉ ሰነድ የሚገባበት አድራሻ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
  • ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200

8. የጨረታ አሸናፊዉ ድርጅት ወይም ግለሰብ የዉል ስምምነት ከተፈረመበት ቀን በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ለየኒቨርሲቲው ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ከከፈለበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ ቀናት ውሥጥ ያሸነፈበትን እቃ ማንሳት አለበት፡፡

9. ዩኒቨርሲቲዉ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ስልክ ቁጥር 011-122-00 01/011-124-32-72 ፖ.ሣ.ቁ 1176 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-30
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-30 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa University
  • Buyer TIN: 0000970957
  • Buyer's registered address: Foreign Purchasing DivisionYekatit 12, Martyr's SquareAddis AbabaEthiopia
  • Bid bond: 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 21, 2026)
  • Posted at: 2026-10-21T08:35:40.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders