Other Sales

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት የኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ከነጄነሬተር ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ሆፕሻይን ትሬዲንግ ኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ከነጄነሬተር በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ከነጄነሬተር ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

 

የተከራዩ ስም

የሚሸጠው ንብረት ዓይነት እና ዝርዝር መረጃ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የዝግ ጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)

ዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ

የዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

የጨረታ ሁኔታ

1

 

 

 

 

 

 

ሆፕሻይን ትሬዲንግ

  1.  Air compressor (01) psc
  2.  Refrigerator Dryer (01) psc
  3. Air purification system (01) set
  4. 95% oxygen generator (01)psc
  5.  99%high purity oxygen generator(01) psc
  6. Oxygen storage tank (01)psc
  7. Buffer thank before oxygen booster/air cooling (psc)
  8. High pressure oxygen booster/air cooling (psc) 
  9. Oxygen control box with touch screen controlling system/fixed on 95% oxygen generator diesel generator (01) set
  10. Filling station (01)psc
  11. AESS/auto vent port/system automatically vent the unqualified oxygen/fixed on 95% oxygen generator(01) set
  12. Cylinder with cap/accessory for medical use/ model 40L/ (100) psc
  13. Spare part (01) set
  14. Diesel generator (01) set ናቸው።

 

 

 

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጋሞ ዞን፣ አርባምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ውስጥ ማምረቻ ማሽኖች በሚገኝበት ሸድ

 

 

 

 

 

 

 

 23,250,000

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን፣ አርባምንጭ ከተማ

 

 

 

 

ህዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 እስከ 6፡00

 

 

 

 

 ዝግ ጨረታ

 

የዝግ ጨረታው መመሪያ

  1. በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻ በመጥቀስ፤ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፤ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ ወይም 20% በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪከት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ገዢው የሚገዘበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል።
  2. ንብረቱ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ አስ/ር፤ ነጭ ሳር ቀበሌ ውስጥ ማምረቻ ማሽኖች በሚገኝበት ሸድ ውስጥ ነው። የዝግ ጨረታ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ፤ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት/በሕግ የተወሰነ ታክስ ጨምሮ የሚጠየቁ ማንኛውንም ከፍያ በቅድሚያ በመከፈል ንብረቱን ይረከባል።
  3. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን ይረከባል። በዝግ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመከፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በዝግ ጨረታ መሳተፍ ይችላል፤
  4. ንብረቱን በከፊል ለመከራየት የሚፈልግ ተጫራች ከሆነ ቢያንስ ያሸነፈበትን ዋጋ 20% ቅድሚያ በመክፈልና የባንኩን የሊዝ ኪራይ መስፈርት በሟሟላት በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ የማሽኔሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። ሆኖም ግን በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የዝግ ተጫራች አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል። ለተሸነፉ ተጫራቾች በጨረታው ያስያዙት የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  5. ንብረቱ በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃዱቤ ግዥና ኪራይ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክቱ ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎች መስማማት ይጠበቅበታል። የዝግ ጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ  ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጠበቅበታል።
  6. የዝግ ጨረታ አሸናፊ የካፒታል ዕቃው ከለበት ቦታ ወደ ሚፈለግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ የጉዞ ኢንሹራንስ፤ ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ይከፍላል።
  7. የዝግ ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ህዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኢትዮጰያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት ሎን ወርከአውት ዲቪዥን ቢሮ ይደረጋል። ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢትዮጰያ ልማት ባንከ አርባምንጭ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር በስልክ ቁጥር 046-181-0606/0303 ደውሎ ማነጋገር ይችላል። ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጨራች ከዝግ ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት አርባምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ማሽኖቹ በሚገኝበት ቦታ/ሼድ/  ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል። ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የዝግ ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-18 10:00
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer's registered address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 20%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 22, 2026)
  • Posted at: 2026-10-22T11:01:33.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders