Other Sales
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር የተለያዩ ንብረቶችን መሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዛቸውን የፍ ማምረቻ ማሽን፤ የልብስ ስፌት ማሽን /ሴንጀር/ የአምፖል ማምረቻ ማሽን የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪና የሞተር ሳይክሎችን ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ- 02/2019
የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ከሊያንችን ፕላስቲክ ፕሮዳክሽን ማኑፋክቸሪንግ፣ ከኤቢሲ ማኒፋክቸሪንግ፣ ከኤሊኤላ ጋርመንትና ጨረቃ ጨርቅ፤ ከFKD Trading፣ ከሰንራይዝ፣ ከኢኑኘሬሳ ኮንስትራክሽን፣ ከፎኔክስ ኢንደስትሪ፣ ከአልቦርድ የሕክምና አገልግሎት፣ ከጋንፋር፣ ከአባቢሊዮን፣ ከብሪልየንት፣ ከካልወርክ፣ ከአፍራን አስመጭና ላኪ፣ ከሜጋ ቪሌጅ ፣ከተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ኃ/ የተ/የግ/ማህበር የተያዙ የተለያዩ የጫማ መምረቻ ማሽን የአምፖል ማምረቻ ማሽን፤ የልብስ ስፌት ማሽን /ሴንጀር/፣ የሕክምና ዕቃዎችን፣ Scaffolding፤ ልዩ ልዩ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ የቢሮ እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን፣ የሞተር ሳይክሎችን እንዲሁም የተለያየ ሞዴል ያላቸው 26 ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00ሰዓት ሕንፃ “መ” 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሕንፃ “ሀ” 2ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል።
- በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ አንድ አስረኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Minstry of Revenue) በባንክ አሠሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።
|
ተቁ |
የመ/ ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ገቢዎች ሚኒስቴር
|
የጫማ ማምረቻ ማሽን እና የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሸከርካሪዎች
|
ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት
|
ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ |
5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቶች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6. የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።
7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
8. የተሸከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፉበትን ሀብት/ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል።
10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
11. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-617-84-90 ኮድ(2044)(2045) (2046) የውስጥ መስመር (EXT) 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MOR.Gov.et መመልከት ይቻላል።
ገቢዎች ሚኒስቴር
Tender details
- Deadline: 2026-11-07
- Bid closing time: 09:45
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45
- Bid opening: 2026-11-07 10:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ministry of Revenue
- Buyer's registered address: የቀድሞ ቡና ቦርድ ከንፋስ ስልክ ት/ቤት ዝቅ ብሎ ባለው ሙለጌ ህንፃ ላይ
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
- Posted at: 2026-10-23T08:09:51.000Z
- Source: Qelal Tenders