Other Sales

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ኦክሲጅን ማምረቻ ማሽን እና የተለያዩ ሲሊንደሮች መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥውስጥ የተጠቀሰውን የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥ እና ኪራይ ተከራይ በውሉ መሰረት ግዴታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዩ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በሐራጅ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል።

የካፒታል ዕቃ ተከራይ ስም

የሚሸጠው ንብረት

 

የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)

ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ

የ ሐ ራ ጅ ደረጃ

 

ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ፣  ቀን እና ሰዓት

አቶ ሀብታሙ አበጋዝ

 

ኦክሲጅን ማምረቻ ማሽን እና የተለያዩ ሲሊንደሮች

 

64,991,747.97

ቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ክ/ከ በተከራዩ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ

2ኛ

በተከራዩ የማምረቻ  ቅጥር ግቢ ውስጥ ህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከ4፡00-6፡00

 ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ እና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የሽያጭ ጨረታው ውጤቱ ይሰረዛል።
  3. ድርጅቶችን በመወከል በሽያጭ ጨረታ ላይ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጠ ዋና የውክልና ስልጣን እና አስፈላጊ ሰነድ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል
  4. የጨረታው አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።
  5. የጨረታው አሸናፊ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
  6. የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያ ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
  7. አሸናፊ ተጫራች ማሽኑን ካለበት ማምረቻ ቦታ መውሰድ አሊያም ከይዞታ ባለቤቱ ጋር መስማማት ይኖርበታል።
  8. ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-211-6687 ላይ መደወል ይቻላል። ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-10
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-11-10 12:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer's registered address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 20%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
  • Posted at: 2026-10-23T09:09:20.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders