Building and Finishing Materials
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው አዳዲስ አልባሳት (ቦርሳዎች) እና የኮንስትራክሽን ማቴርያል በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ግ-07/2019 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው አዳዲስ አልባሳት (ቦርሳዎች) እና የኮንስትራክሽን ማቴርያል በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣
1.ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና ጨረታው የሚያበቃበት ቀን እና ሰዓት
የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-
|
ተቁ
|
የእቃው አይነት |
ጨረታው አይነት
|
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን |
ጨረታው የሚከሄድበት ቀን
|
ጨረታው የሚዘጋበት ሰዓት
|
ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት
|
ስልክ ቁጥር
|
|
1 |
አዳዲስ አልባሳት (ቦርሳዎች)
|
ግልፅ
|
13/02/2019 |
20/02/2019 |
4:00
|
4:30
|
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
2 |
የኮንስትራክሽን ማቴርያል
|
ግልፅ
|
13/02/2019 |
20/02/2019 |
4:00
|
4:30
|
022 111 8429/ 022 211 8925 |
5. በግልፅ ጨረታ ሽያጭ ላይ የእቃዎቹ አስመጪ ወይም የአስመጪ ቤተሰብ መሳተፍ አይችሉም። ነገር ግን በጨረው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ።
6. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለ (CPO) (Customs commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
7. በግልጽ ጨረታ ለመሽጥ የወጡት የኮንስትራክሽን ማቴርያል በአዳማ ከተማ በሬቻ አከባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ቁጥር 1 እንዲሁም አዳዲስ አልባሳት( ቦርሳዎች) በአዳማ ቆርቆሮ አከባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው መጋዘን ቁጥር 3፣ 4 እና 5 ውስጥ ሲሆን ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል ።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ፤ ለተሽናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
10. ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
11. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
12. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11- 551/ 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ / ቅ/ ጽ / ቤት የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 022 111 8429 እና 022 211 8925 ደውሎ
መጠየቅ ይቻላል።
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ ጽ / ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-30
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-30 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%)
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
- Posted at: 2026-10-23T09:44:46.000Z
- Source: Qelal Tenders