Other Sales

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በመጋዘን የተጠራቀሙ ጋዜጦችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የንብረት ማስወገድ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በመጋዘን የተጠራቀሙ ጋዜጦችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒ በመያዝ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

1. ተጫራቾች ለሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በመምጣት መግዛት ይቻላል።

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

3. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒና የሚወዳደሩበትን ዋጋ በአንድ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ በመስሪያ ቤቱ አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሑፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ንብረቶችን ማንሳት ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ባያነሳ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረስበታል።

5. ማንኛውም ተጫራች በሌላው ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማስገባት አይችልም።

6. ድርጅታችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 11-08-80-99 ወይም 09 13-21-50-37

አድራሻ፡- 4 ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-30
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-10-30 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Press Agency
  • Buyer's registered address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 50.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 25, 2026)
  • Posted at: 2026-10-26T08:15:37.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders