Building and Finishing Materials

ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ/የተ/ግ/ማህበር (ኖክ) በቃሊቲ መጋዘን ውስጥ የሚገኙትን ባለ 1ኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ ፓሌቶች፣ ኤምዲኤፍ መደርደሪያዎችና ቦርዶች፣ ስብርባሪ እንጨቶች እና የተለያዩ ፕላይዉዶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ጉዳዩ፡- ጨረታን ይመለከታል፡፡

ኩባንያችን ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን ባለ 1ኛ ደረጃ ፣2ኛ ደረጃ ፓሌቶችን ፣ ኤምዲኤፍ መደርደሪያ (MDF shelf)፣ ኤምዲኤፍ ቦርድ (MDF) sheet፣ ስብርባሪ እንጨቶች እና የተለያዪ ፕላይዉድ (Plywood) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። የእቃው ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል።

ተ.ቁ

የፓሌት ዓይነት

ብዛት

1

1ኛ ደረጃ ፓሌት (ቀይ)

60

2

2ኛ ደረጃ ፓሌት

160

3

ኤምዲኤፍ መደርደሪያ (MDF shelf)

5

4

ኤምዲኤፍ ቦርድ (MDF sheet)

ባለበት በጠቅላላ

5

ስብርባሪ እንጨቶች

ባለበት በጠቅላላ

6

ፕላይዉድ (Plywood) (1.2m × 2.3m)

1,320

7

ፕላይዉድ (Plywood) (1.1m x 1.1m)

2,400

8

ፕላይዉድ ኮምፐርሳቶ (Plywood) (1.2m × 2.3m × 2mm)

80

9

ፕላይዉድ ፋይዚት (Plywood) 1.2m × 2.3m

310

ስለሆነም ድርጅታችን ከላይ የተዘረዘሩትን የእንጨት ውጤቶች ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል። በተጨማሪም ተጫራቾች ፓሌቶቹን እንደከዚህ ቀደም መምረጥ እንደማይችሉ ከወዲሁ ማሳሰብ ይወዳል። ከላይ ለተጠቀሱት እቃዎች ዋጋ በመስጠት መወዳደር ይቻላል። እቃዎቹን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜን ጨምሮ ቦታው ላይ በመመልከት የሚገዙበትን ዋጋ ከ15 በመቶ ቫት ጋር በመግለጽ ድርጅቱ ለዚህ ጨረታ ያዘጋጀውን ፎርም በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል። ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው ሊሆን ይገባል። እንዲሁም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማቅረብ መጫረት ይቻላል።

አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ በተገለጸለት በሦስት የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን በአንድ ጊዜ ክፍያ መፈጸም ይኖርበታል። ይህንን ባይፈጽም ለጨረታው ያስያዘውን ገንዘብ በሙሉ የማይመለስ በመሆኑ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል። አሸናፊ እቃውን በሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድን ሳይጨምር) ከቃሊቲ መጋዘን ማንሳት አለበት። ይህ ባይሆን የመጋዘን ኪራይ በቀን 3,000.00 ብር ይከፍላል። ሙሉ ክፍያ ሲፈጽም እና ሙሉ በሙሉ እቃዎቹ ከቃሊቲ መጋዘን ሲነሱ ብቻ ሲፒኦው ተመላሽ ይሆናል።

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁ. 011-618-7165 ወይም 011-439-0378 መደወል ይቻላል።

አድራሻ፡- ቦሌ ኤርፖርት መንገድ ከፍሬንድሺፕ ህንፃ ፊት ለፊት ያለው የኖክ ዋ/መስሪያ ቤት

ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ማህበር (ኖክ)


Tender details

  • Deadline: 2026-10-31
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜን ጨምሮ
  • Bid opening: 2026-10-31 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: National Oil Ethiopia PLC
  • Buyer TIN: 0000059459
  • Buyer's registered address: ቦሌ ኤርፖርት መንገድ ከፍሬንድሺፕ ህንፃ ፊት ለፊት ያለው የኖክ ዋና መስሪያ ቤት
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Published on: Qelal Tenders (Oct 27, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T08:21:56.000Z
  • Buyer website: https://www.nocethiopia.com/
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders