Other Sales

ሜጋ ማተሚያ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ የብረት ጠረጴዛዎችና ሼልፎች፣ የእንጨት ጠረጴዛዎችና ሼልፎች፣ የተለያየ ጣውላና ብረት፣ የተለያዩ ፋይል ካብኔቶች፣ የተለያዩ በሮች፣ ተሽከርካሪ ዲስፕለይ፣ ሚዛን ወዘተ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ሜማ/12/2/19

ኩባንያችን ሜጋ ማተሚያ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ የብረት ጠረጴዛዎችና ሼልፎች ፣ የእንጨት ጠረጴዛዎችና ሼልፎች፣ የተለያየ ጣውላና ብረት ፣ የተለያዩ ፋይል ካብኔቶች፣ የተለያዩ በሮች፣ ተሽከርካሪ ዲስፕለይ ፣ ሚዛን ወዘተ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡

1. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ሜጋ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች እቃውን በአካል በመቅረብ ገርጂ ሜታ አካባቢ በሚገኘው የድርጅታችን መጋዝን በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 2/3/2019 ዓ፡ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ለዚህ ተብሎ በሜጋ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 217 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው ፡፡

4. አንድ ተጫራች መግዛት የሚፈልገውን ከአንድ በላይ የእቃ ምድብ ከሆነ ለሚጫረተው ለእያንዳንዱ የእቃ ምድብ ዋጋ መጥቀስ አለበት፡፡

5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የእቃ ምድብ የሚጫረቱበት አጠቃላይ ዋጋ አስር በመቶ በሜጋ ማተሚያ ኃላ.የተ.የግ.ማ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ጨረታውን ላላሸነፉት ብቻ የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ይመለስላቸዋል፡፡

7. የጨረታውአሸናፊ/ዎች ቀሪውን ገንዘብ በአምስት /5/ የሥራ ቀናት ውስጥ አጠቃለው ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ በዚህ ግዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ከፍለው ንብረቱን የማያነሱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅታችን ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡

8. ጨረታው በ2-3-2019 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ2/3/2019ዓ.ም ልክ ከቀኑ 7፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሜጋ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች አለመገኘት ጨራውን ከመክፈት አያግደውም፡፡

9. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨራውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሕጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቦሌ ሜጋ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 217

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913 729 631

ሜጋ ማተሚያ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-11
  • Bid closing time: 13:00
  • Bid opening: 2026-11-11 13:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mega Printing P.L.C.
  • Buyer TIN: 0000038949
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T08:47:28.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders