Spare Parts and Car Decoration Materials
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል
Spare Parts and Car Decoration MaterialsEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and Electronics
Amhara
More tags
Office FurnitureFurniture and FurnishingComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesStationeryMetal and Metal WorkingOther MetalsSteel, Metals and AluminiumOther SalesSales, Disposals and ForeclosureDisposal SaleSteel Raw Materials and ProductsAmharic2merkatoAmhara Region Police Commission
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2019
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን
- ሎት 01. የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣
- ሎት 02 የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን እና
- ሎት 03 ጎማና ባትሪ በጠቅላላ ድምር በሎቱ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ማንኛዉም የታደሰ ብሄራዊ መታወቂያ ያለዉ ግለሰብ ወይም ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለዉ ድርጅት ሊሳተፍ ይችላል፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ የተጫራቾች መመሪያውንና የሚሸጡ ንብረቶችን ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ለእያንዳንድዱ ዝርዝር ሰነድ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በአማራ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋው 2 በመቶ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ከፈለጉ ማስረጃውን ወይም የገቢ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከፋይናንስ (ዋጋ ማቅረቢያ) ጨረታ ሰነድ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ማህተማቸውንና ፊርማችን በማሰፈርና ፖስታውን በሚገባ በማሸግ የአማራ ፖሊስ ዋናዉ መስሪያ ቤት ግዥ ባለሙያዎች ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ድረስ ገቢ በማድርግ በእለቱ 11፡30 ላይ ይዘጋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሸጡትን የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን በተቋሙ እስቶር በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ዘወትር በስራ ስአት ከሰኞ አስከ አርብ ማየትና መገምገም ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ አሸናፊነቱ ከተገለፀት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ያሸነፋቸዉን እቃዎች ማንሳት ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 77 13 56 78 ባህርዳር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት
ባህር ዳር
Tender details
- Deadline: 2026-11-16
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-17 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Region Police Commission
- Buyer's registered address: ባህር ዳር ቀበሌ 16 ከቴሌና ሲቪል ሰርቪስ ማዕከል አብክመ ልዩ ሃይል ፖሊስ ም/ዘርፍ ግዥ ቢሮ ቁጥር 11
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Be'kur (Nov 02, 2026)
- Posted at: 2026-11-03T12:54:21.000Z
- Source: Qelal Tenders