Other Sales
ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. የተለያዩ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን (ሎት 1 - የሰብል ሽያጭ፣ ሎት 2 - ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ፣ ሎት 3 - የሩዝ መፍልፍያ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች፣ እና ሎት 4 - የሩዝ መፍልፍያ ማሽን የጥገና ሥራ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.
- ሎት 1.የሰብል ሽያጭ፣
- ሎት 2. ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ፣
- ሎት 3.የሩዝ መፍልፍያ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች፣
- ሎት 4. የሩዝ መፍልፍያ ማሽን የጥገና ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሽናፊው መግዛትና መሽጥ ይፈለጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያ ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 (ሶስት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ቅዳሜ ዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፡፡ አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ የሎት አራት አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡ አሽናፊው የአሸነፈውን እቃ በፍትህ ውል ከተመርመረ (ከተመዘገበ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል/፡፡
- አሽናፊው የአሽነፈውን የሚገዙ ዕቃዎችን በእራሱ ትራንስፖረት አጓጉዞ ሊያቀርብ ሲሆን የሚሽጡ ዕቃዎችን የስራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ አሸናፊ ይሸፍናል፡፡ ማንኛውም የሚገዙና የሚሽጡ እቃዎች መጠንና (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
- በሎት 2 ላይ የተጠቀሱት አሮጌ ያገለገሉ ዕቃዎች ውስጥ ከሎት 1ሀ እሰከ ሎት 1ሐ ደረስ በሶስት ደረጃ የተመደበ ስለሆነ ከሎት 1ሀ እሰከ ሎት 1ሐ ድረስ የፈልጉትን መርጦ መሙላት ይቻላል፡፡ የሰበል ሸያጭ የሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዝን ሲሆን የሩዝ ሰብል ሽያጭ የሚገኝበት ቦታ ሐሙሲት መጋዝን ሲሆን አሽናፊው መጋዝን ላይ ያለውን ሰብል ለማንሳት ፈቃድኛ የሆነ እና ጥራቱን በአካል በማየት መሙላት የሚቻል ሲሆን ሰብል ሽያጭ የተለያየ አይነት ሰለሆነ ሁሉንም ወይም መርጦ መሙላት ይቻላል፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሃሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /058 320 16 70 መጠይቅ ይችላሉ፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.
Tender details
- Deadline: 2026-11-12
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን 8፡00
- Bid opening: 2026-11-12 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን 8፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Merekeb Farmers' Cooperative Union
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 350.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ ብር)
- Published on: Be'kur (Nov 02, 2026)
- Posted at: 2026-11-03T13:41:05.000Z
- Source: Qelal Tenders