Other Sales

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተያዙና የተወረሱ የተለያዩ ዕቃዎች ሽያጭ
ማስታወቂያ ቁጥር 19/2019

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፤ ሞባይሎች፤ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን 1 የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፤ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ህዳር 10/209 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በኦክሸን ኢትዬጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et  ላይ በሚተርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ወይም ድህረ ገጽ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕስቶር ወይም : ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በመሆኑም

1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ : ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ፎቶ በማንሳት ስካን በማድረግ) ኦንላይን የኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et  ማያያዝ ይኖርበታል።

2. በጨረታው ላይ የዕቃው ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።

3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ህዳር 10/2019 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን እክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et  ላይ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ዕ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMSSON ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተዉ ያሰሩትንም ሲፒኦ በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መሬት ይችላሉ። 

5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

 

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

 

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1.

 

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

የእቃ ግልፅ

 

እስከ 15/03/2019

 

16/03/2019 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል።

6. የጨረታ መክፈቻ ቦታ ሙሉ በሙሉ የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et  (በኦንላይን) የሚካሄደ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ።

7. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት ተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንነት ይኖርባቸዋል።

9. ከላይ በተ.ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ዉስጥ ከፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

10. መ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት
በስልክ ቁጥር 09 05 11 55 11
አድራሻ:- ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 (ኦክሽን ኢትዮጵያ)
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ 011 470 8503

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ሠደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ሠደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ ጽ / ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-25
  • Bid closing time: 09:45
  • Bid opening: 2026-11-25 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T13:13:33.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders