Generators
የአገዉ ግ/ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ጀኔሬተር ለሶስተኛ ጊዜ በግልጽ ማስታወቂያ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የጀኔሬተር ሽያጭ ግልጽ ማስታወቂያ
የአገዉ ግ/ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በድርጅቱ የዉሃ መገኛ ቦታ ላይ የሚገኙትን ጀኔሬተር ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ በበኩር ጋዜጣ ያወጣ ቢሆንም ባለመሸጡ ለሶስተኛ ጊዜ በግልጽ ማስታወቂያ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
- ጨረታዉ ለማንኛዉም ተጫራች ክፍት ነዉ፡፡
- የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩት ከጠቅላለ ዋጋ የሚመለስ 5 በመቶ ብር 75,000 (ሰባ አምስት ሺህ ብር) በተረጋገጠ ባንክ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ (ቢድ ቦንድ) ማስያዝ አይፈቀድም፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በድርጅታችን ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታ ፖስታ ጋር ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱን ከአገዉ ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከገቢ፣ ግዥ፣ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለዉ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ መነሻ ዋጋ ብር 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) ሲሆን ዝርዝር መግለጫዉ ሰነዱ ላይ ያለ በመሆኑ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ህዳር 07/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ህዳር 21/2019 ዓ.ም 11፡00 ድረስ በስራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን ጨረታዉ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ ህዝባዊ በዓል ከሆነ ግን በቀጣዩ ቀን ፖስታዉ ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበትና ባይገኙም ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሆነዉ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ክፍያዉን በድርጅቱ ባንክ አካዉንት ከፍለዉ ደረሰኝ በማቅረብ እና ዕቃዉን እስካለበት ሳይት ድረስ በመሄድ ንብረቱን መረከብ ይችላሉ፡፡ በተጠቀሰዉ ቀን ክፍያ ባይፈጽሙ የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ የሚጠቀም መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- አሸናፊ የሚለይበት ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ብቻ ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁር 058 224 04 62 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አገ/ግ/ቤት/ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-12-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-12-01 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Agew Water and Sewerage Authority
- Bid bond: 5 በመቶ ብር 75,000 (ሰባ አምስት ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T14:20:37.000Z
- Source: Qelal Tenders