Other Sales

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ያገለገሉ ዕቃዎች ዝርዝር

ዕቃው የሚገኝበት ቦታ

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ሰ.ፒ.ኦ (ብር)

ቁርጥራጭ ብረቶች ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው ጎማዎች፤ የመኪና ባትሪዎች የዉህ ሮቶ አሮጌ በርሜል የብረት የተለያዩ የእስቴሽነሪ ዕቃዎች ፣ የተለያየ መጠን ያላቸው ጀሪካኖች ፤ የፕላስቲ ከሬቶች፤ የግሪን ሀጢስ ፕላስቲክ ፤ ፕላስቲክ በርሚል ፣ የተለያየ መጠን ያላቸው ማዳበሪያ፤ የተለያየ መጠን ያላቸዉ የኬሚካል እቃ ፤ የእርሻ መገልገያ መሳሪያዎች ፤ ትራክተሮች፤ እና የውሃ ፓምፕ ወዘተ እቃዎች

ሎት 1. ኤልፎራ ቢሾፍቱ ጂቱ(ቢሾፍቱ)

ሎት 2 ኤልፎራ ቢሾፍቱ ፖልትሪና ቄራ (ቢሾፍቱ)

ሎት 3 ወንጂ ኩሩፍቱ (ወንጂ)

ሎት 4. ኤልፎራ ሻሎ እርሻ (ሀዋሳ ሻሎ)

ሎት 5 ጨፋ የተቀናጀ እርሻ (ጨፋ)

በእያንዳንዱ ሎት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ)

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ አሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾ አዲስ አበባ ላይ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ጉርድ ሾላ (ላምበረት) አካባቢ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት መግዛት ይችላሉ የጨረታ ሰነዱ መግዣ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ነው::

3. ተጫራቾች ዋጋ ከመስጠታቸው በፊት ዕቃዎች በሚገኙበት ከተማ በአካል በመገኘት ማየት ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለጨረታ ማስከበሪያ/Bid bond/ የሚሆን ብር ከላይ የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ማቅረብ አለበት።

5. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለጹትን ፎርማሊቲዎች በማሟላት በዚሁ ፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን መለያ ኮድ (ሎት) እና ቦታ በፓስታው ላይ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡

7. ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ውጤቱ እንደታተመ ተመላሽ ይደረጋል።

8. ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር ለ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት በኤልፎራ ዋናው መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ገበያና ሽያጭ አገልግሎት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ፖስታቸውን እንዲያስገቡ ይደረግና፤ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት የጨረታው ሣጥን ይታሸጋል፡፡ ከዚያም በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ውስጥ ጨረታው ይከፈታል፡፡

9. ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-09 54 49 53 63 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 13:30
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር ለ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ቆይቶ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ በ7፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-26 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር ለ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ቆይቶ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ELFORA Agro Industries P.L.C.
  • Bid bond: 200,000.00 ብር በእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
  • Posted at: 2026-11-17T09:43:54.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders