Spare Parts and Car Decoration Materials

በልስቲ ኢንዱስትሪያል ኃ.የተ.የግል ማህበር አማራ ክልል ደጀን የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ንብረቶች ሽያጭ የወጣ ማስታወቂያ

በልስቲ ኢንዱስትሪያል ኃ/የተ/ የግል ማህበር አማራ ክልል ደጀን ታይም ጅፕሰም ፋብሪካ ግቢ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም የተሸከርካሪና ማሽነሪ ጎማዎችን፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የተቃጠለ ዘይት፣ባትሪዎች፣ የብረት በርሚል እና የጅብሰም ከረጢቶች...ወዘተ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የቀረቡትን መስፈርቶች የምታሟሉ ጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።

2. የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታው ጠቅላላ ዋጋ 5% በC.P.O ማስያዝ አለባቸው።

3. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ውል ማስከበሪያ (Performance Guaranty) ያሸነፈውን ዋጋ 5% በC.P.O ማስያዝ ማስያዝ አለበት።

4. ተጫራጮች እያንዳንዱ ለሽያጭ የቀረበ ንብረት ዋጋ በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።

5. የቀረበው ዋጋ 15% (ቫት) ያካተተ መሆኑንና አለመሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታው አሸናፊ ጨረታው ላይ የተዘረዘሩትን ንብረት ካሸነፈበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ሳምንት ውስጥ በራሳቸው ማጓጓዣ ከበልስቲ ደጀን ታይም ጅፕሰም ግቢ ኢንዱስትሪያል ማንሳት አለባቸው::ማንሳት ካልቻሉ ቀደም ብሎ ያስያዙትን ውል ማስከበሪያ (Performance Guaranty) ብር ገቢ ተደርጎ ለሁለተኛ አሸናፊ ይሰጣል (ጨረታው ይሰረዛል)።

7. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ በታሸገ ኢንቬሎፕ ቦሌ(ማተሚያ ጀርባ)  በሚገኘው ኢትዮ-ቤስት ሪልእስቴት ታወር 5ተኛ ፎቅ በተዘጋጀ ሳጥን እንዲሁም ደጀን በሚገኘው ታይም ጅፕሰም ፋብሪካ ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም ጠዋት 3:30 ማስገባት አለባቸው።

8. ጨረታው ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ10ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።

10. ተጫራቾች ለሚፈልጉት ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0940444466 ወይም 0911248136 በስራ ሰዓት በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

11. ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በልስቲ ኢንዱስትሪያል ኃላ/የተ/ የግል ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-08-31 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Belsty Industrial PLC
  • Bid bond: 5%
  • Published on: Reporter (Aug 19, 2026)
  • Posted at: 2026-08-19T13:17:51.000Z
← Back to all tenders