Other Sales
በልስቲ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር አዲስ አበባ ታጠቅ ግቢ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ንብረቶች ሽያጭ የወጣ ማስታወቂያ
በልስቲ ትሬዲንግ ኃ/የተ/ የግል ማህበር አዲስ አበባ ታጠቅ ግቢ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም የተሸከርካሪና ማሽነሪ ጎማዎችን፣ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የተቃጠለ ዘይት፣ባትሪዎች እና እንጨቶች...ወዘተ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የቀረቡትን መስፈርቶች የምታሟሉ ጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
2. የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታው ጠቅላላ ዋጋ 5% በC.P.O ማስያዝ አለባቸው።
3. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ውል ማስከበሪያ (Performance Guaranty) ያሸነፈውን ዋጋ 5% በC.P.O ማስያዝ አለበት::
4. ተጫራጮች እያንዳንዱ ለሽያጭ የቀረበ ንብረት ዋጋ በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።
5. የቀረበው ዋጋ 15% (ቫት) ያካተተ መሆኑንና አለመሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው አሸናፊ ጨረታው ላይ የተዘረዘሩትን ንብረት ካሸነፈበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ሳምንት ውስጥ በራሳቸው ማጓጓዣ ከበልስቲ ትሬዲንግ ግቢ ማንሳት አለባቸው::ማንሳት ካልቻሉ ቀደም ብሎ ያስያዙትን ውል ማስከበሪያ (Performance Guaranty) ብር ገቢ ተደርጎ ለሁለተኛ አሸናፊ ይሰጣል (ጨረታው ይሰረዛል)።
7. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ በታሸገ ኢንቬሎፕ ቦሌ(ማተሚያ ጀርባ) በሚገኘው ኢትዮ-ቤስት ሪልእስቴት ታወር 5ተኛ ፎቅ በተዘጋጀ ሳጥን ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም ጠዋት 3:30 ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ10ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
10. ተጫራቾች ለሚፈልጉት ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111561805 ወይም 0944308793 በስራ ሰዓት በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
11. ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በልስቲ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/ የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-29
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-08-31 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: BELSTY TRADING PLC
- Buyer TIN: 0004800986
- Bid bond: 5%
- Published on: Reporter (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T13:24:16.000Z