Other Sales

የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በፋብሪካው ግቢ በምርት ሂደት ላይ የሚመረቱ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ክፍል 1 ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በፋብሪካው ግቢ በምርት ሂደት ላይ የሚመረቱ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን በተለያየ ክፍልፋይ (ሎት) ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መረጃ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የተረፈ ምርቶቹን አይነት እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታው መመሪያ ሰነድ ማግኘት ይቻላል ወይም በፋብሪካው ቦታ ላይ በአካል በመገኘት ማየት ይቻላል፤

የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ 200 ብር ከፍሎ መግዛት ይቻላል።

1) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በጨረታው መመሪያ ላይ በተገለፀው የብር መጠን መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በሲፒኦ(CPO) ማስያዝ አለባቸው።

2) ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋውን እና አስፈላጊ መረጃዎችን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 02፡00 እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3) ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የካላንደር ቀናት አየር ላይ ይሆናል፤ሆኖም ግን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።

4) የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ወይም በማግስቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ይከፈታል።

5) ተጫራቾቹ ከሥራ መስኩ ጋር ተያያዥነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የVAT እና TIN ሰርተፊኬት የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፤ በውክልና የሚወዳደሩ አካላት ከፍትህ ወይም ከሰነዶች ማረጋገጫ ህጋዊ የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።

6) መሥሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0920 322 355 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-10-06 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debrhe Berhan Wood Processing P.L.C
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T07:19:18.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders