Other Sales
ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አክሲዮን ማህበር ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ቅዱስ ሚካኤል ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ የአ/ማህበሩ የጥገና ማዕከልና መጋዘን ዉስጥ የሚገኙ ያገለገሉ ጎማዎች፣ የተቃጠለ ዘይት፣ ብረታ ብረቶች፣ መለዋዎጫ እቃዎችና የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አክሲዮን ማህበር ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ቅዱስ ሚካኤል ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ የአ/ማህበሩ የጥገና ማዕከልና መጋዘን ዉስጥ የሚገኙ ያገለገሉ ጎማዎች የተቃጠለ ዘይት ብረታ ብረቶች መለዋዎጫ እቃዎችና የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
ስለሆነም፡- አ/ማህበሩ ከላይ የተጠቀሱትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ስለሚፈልግ በጨረታዉ መሳተፍ ለሚፈልግ ማንኛዉም ተጫራች ከዚህ በታች በተገለፀዉ የጨረታ መመሪያ መሠረት መሳተፍ ይችላል::
1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ስዓት ከ2፡30-11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ 2፡30-6፡30 የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በአ/ማህበሩ ዋና መ/ቤት መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ማግኘት ይችላሉ::
2. ተጫራቾች ንብረቶቹ በሚገኙበት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያ ፊት ለፊት ቅዱስ ሚካኤል ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ የድርጅቱ ጋራጅ ዉስጥ በመገኘት ከመስረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ሰዓት መመልከት ይችላሉ::
3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ንብረት የጨረታ ማስከበርያ (ቢድ ቦንድ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሽህ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) በ Selam Bus Line Share Company ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ስምና ስልክ ቁጥር በመፃፍ በድርጅቱ ጋራጅ ዉስጥ ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል::
5. ጨረታዉ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ9፡15 በድርጅቱ መሰብሰብያ አዳራሽ ይከፈታል::
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መግለፅ አለባቸዉ፤በሁለቱ _ ልዩነት ካለ ከፍተኛዉ ዋጋ ይወሰዳል::
7. በጨረታዉ አሸናፊ የሚሆነዉ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል::
8. ተጫራቾች አሽናፊነታቸዉ ከተነገራቸዉ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ 10 የስራ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያ በመክፈል ንብረቱን ማንሳት ይኖርባቸዋል::
9. በጨረታዉ ያላሸነፉ ተጫራቾች አሸናፊዉ ከተለየ በኋላ ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል::
10. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት::
11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
ለተጨማሪ መረ ጃ ፡-
በስልክ ቁጥር 09-75-23-27-10 // 09-14-61-25-98 /011-515-86-96 // 011-470-83-82 ደውለዉ ይጠይቁ::
Tender details
- Deadline: 2026-10-09
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-10-09 15:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Selam Bus Line Share Company
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
- Posted at: 2026-09-28T14:09:44.000Z
- Source: Qelal Tenders