Other Sales

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች፣ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ እቃዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸሮች፣ የተቃጠለ የሞተር ዘይት ከነበርሜሉ፣ የአልሙኒየም ቁርጥራጭ እና የተለያዩ ያገለገሉ ካርቶኖችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ቁጥር 03/2026/27

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች ያገለገሉ የተሽከርካሪ ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች፤ የተለያዩ የተሽከርካሪ እቃዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸሮች፣ የተቃጠለ የሞተር ዘይት ከነበርሜሉ፣ የአልሙኒየም ቁርጥራጭ እና የተለያዩ ያገለገሉ ካርቶኖችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሚገኝበት ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከመስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ያገለገሉ ንብረቶችን ከመስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ያገለገሉ ንብረቶችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ እንዲሁም የተቃጠለ የሞተር ዘይቱን ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ /የቀድሞው አማልጋ ሜትድ/ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል።

3. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።

4. ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሚገኝበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል።

5. የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች እና የተቃጠለ የሞተር ዘይት ምድቦች ላይ የሚሳተፍ ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ ከኢፌድሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተሰጠውን ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የተቃጠለ የሞተር ዘይት የማስወገድ ወይም መልሶ የመጠቀም ፈቃድ ማቅረብ የሚችል ብቻ መሆን አለበት።

6. ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሚገኝበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ በግልጽ ይከፈታል።

7. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-10-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-15 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Commercial Bank of Ethiopia
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T14:56:23.000Z
  • Buyer website: https://www.combanketh.com
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders