Fuel and Lubricants

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ያገለገሉ ንብረቶች ማለትም ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችንና ባትሪዎችን፣ የተቃጠለ ዘይት ከነበርሜል፣ ባዶ ድፍን በርሜሎችን፣ ያገለገለ የመዳብ ሽቦዎችን፣ የሽቦ አልጋዎችንና ፍርስራሽ እንጨቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶች ማለትም ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችንና ባትሪዎችን፣ የተቃጠለ ዘይት ከነበርሜል፣ ባዶ ድፍን በርሜሎችን፣ ያገለገለ የመዳብ ሽቦዎችን፣ የሽቦ አልጋዎችንና ፍርስራሽ እንጨቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ግቢ፣ በግብዓት የተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ ጋራዥና ግቢ ዉስጥ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ። የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ጨረታውም በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ02/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የመሰባሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረተለት ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ንብረት የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ(ተ.ዕ.ታ) ጋር አንድ ላይ በማድረግ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በዝርዝር በማመላከት ማቅረብ አለባቸው።

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ: አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ ከፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ጀርባ ወይም EBG /VOLVO ቀጥሎ ወደ ውስጥ በሚያስገባው መንገድ 100Mገባ ብሎ፤

ስልክ ቁጥር፦ 0920577343: 0915576869 0911166473

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-12
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-12 15:00
  • Bid opening (note): በ02/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
  • Buyer address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 30, 2026)
  • Posted at: 2026-09-30T11:16:47.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders