Other Sales

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባል የሆነው ድርጅታችን ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተወሰነ የግል ማህበር ለሥራ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተቃጠለ ዘይቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ.የተ የግል ማህበር

MIDROC Construction Ethiopia PLC

Document No: MCE/FORM/5/348

አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባል የሆነው ድርጅታችን ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ የተወሰነ የግል ማህበር ለሥራ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተቃጠለ ዘይቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

በዚሁ መሠረት፡-

1. ተጫራቾች አዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ከመካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ከኩዊንስ ሱፐርማርኬት ቀጥሎ ባለው የኢትዮ አግሪሴፍት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት በሚገኘው ህንፃ 3ኛ ፎቅ የድርጅቱ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በአካል በመቅረብ የምትወዳደሩበትን የአንድ ሊትር ዋጋ ከቫት በፊት ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

2. በጨረታው ለመሣተፍ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሆን ይችላል በጨረታ የሚተፈው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ከፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተቃጠለ ዘይት የመሰብሰብ የማጓጓዝ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል (Recycling) ፍቃድና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

3. በጨረታው ለመሣተፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅትና በበጀት ዓመቱ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰነድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰነድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በጨረታው ለሚሳተፉባቸው ዘይቶች ለጨረታ ያቀረቡትን ጥቅል ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማስያዝ ይኖርበቸዋል፣

5. ተጫራቾች ቃሊቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከመስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ባሉት ስድስት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የተቃጠለ ዘይቱን በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የሚገዙበትን የተቃጠሉ ዘይቶች የአንድ ሊትር ዋጋ ከቫት በፊት በመጥቀስ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰአት ከመስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከመስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ረፋድ 4፡00 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ የንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የዋጋ ማቅረቢያና ሲፒአ በሰም በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ። ጨረታው መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ጠዋት ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል።

7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የተቃጠለ ዘይት ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግ ንብረቱን ማንሳት ሲኖርበት ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO የማይመለስ ይሆናል።

8. ኣሸናፊ ድርጅት ግለሰብ የተቃጠለ ዘይቱን የመጫን የማጓጓዝ እና ሌሎች ተዛማጅ ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል።

9. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጫራች እንዲመለስ ይደረጋል።

10ሻጭ ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው

አድራሻ፡- ልደታ ክፍለ ከተማ መካኒሣ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ኢትዮ አግሪሴፍት ቅጥር ግቢ ውስጥ

ማሳሳቢያ

  • ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251 911127478 +251 911900960/+251919487762 ይጠቀሙ
  • ተጫራቾች ሙሉ አድራሻ እና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል።

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-07 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Midroc Investment Group
  • Buyer address: የካ አባዶ ኮንደሚንየም መግቢያ ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ ማኅበር ቅጥር ግቢ
  • Bid bond: 10%
  • Published on: Reporter (Sep 30, 2026)
  • Posted at: 2026-09-30T12:27:40.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders