Steel Raw Materials and Products
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር/EEP/DS/02/19
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፤
- ሎት 1 ምዕራብ ሪጅን (ሻምቡ፣ ጊምቢ፣ ደዴሳ፣ ባኮ፣ ጊዳሚ) ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ቁርጥራጭና ስክራፕ
- ሎት 2 በግልገል ጊቤ ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ቁርጥራጭና ስክራፕ፣ ተሸከርካሪ እና ማሽነሪ
- ሎት 3 ምስራቅ 2 ሪጅን (ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ፊቅ፣ደገሃቡር) ማከፋፈያ ጣቢያ እና ድሬዳዋ ዲዝል ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ቁርጥራጭና ስክራፕ
- ሎት 4 ደቡብ ምዕራብ ሪጅን (ጂማ 1 እና 2፣ መቱ፣ ጋምቤላ፣ በደሌ፣ አጋሮ፣ ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ግልገል ጊቤ) ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ቁርጥራጭና ስክራፕ
- ሎት 5 ጄኔሬሽን ቢዝነስ ስር የሚገኙ ኃ/ማመንጫ (አዋሽ 2 እና 3፣ ቆቃ፣ እና አዳማ 2) ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ ቁርጥራጭና ስክራፕ
- ሎት 6 አዲስ አበባ ኮተቤ ብረታ ብረት ዋና መ/ቤት ግቢ አገልግሎት የሰጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ጎማ
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹም ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል።
- ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት የተቋሙ ጣቢያዎች በመገኘት መመልከት ይቻላል፤
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች ከሎት አንድ እስከ ሎት አምስት ላይ ለመሳተፍ በብረት አቅላጭነት በኢንድስትሪሚንስቴር መመዝገባችሁ የሚያሳያ መረጃ፣ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከ03/02/19 እስከ 18/02/2019 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡00 ድረስ ይካሄዳል ስለሆነም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
- በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ በሚገለፅላችሁ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት መፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፤
- ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ሊሰረዝ ይችላል፤
- ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያን በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68 -828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 011-558-14-24 ወይም 011-558-06-49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
Tender details
- Deadline: 2026-10-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-28 10:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Electric Power
- Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T09:15:02.000Z
- Source: Qelal Tenders