Other Sales
ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር በተለያየ ምክንያት በኩባንያው ስቶር ውስጥ እና ከስቶር ውጪ የተከማቸ የተለያየ ሞዴል መኪኖች መለዋወጫ፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጨረታ ማስታወቂያ
ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በተለያየ ምክንያት በኩባንያው ስቶር ውስጥ እና ከስቶር ውጪ የተከማቸ የተለያየ ሞዴል መኪኖች መለዋወጫ፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች በተገለፀው የጨረታ መመሪያ መሠረት እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተለያየ ሞዴል መኪኖች መለዋወጫ፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን በሚገኙበት ኮምቦልቻ ጋራዥ እና አዳማ ቅ/ፍ ስቶር ዘወትር በሥራ ሰዓት በመሄድ የገዙትን ጨረታ ሰነድ በማሳየት ስፔር ፓርቱን በአካል ማየት ይቻላል።
2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በጨረታ ሠነዱ ላይ የሞሉትን ዋጋ የጠቅላላ ድምሩ 2% ጨረታ ማስከበሪያ / ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማስገባት ውድድሩን መሳተፍ ይቻላል።
3. ሌላው በሚያቀርበው የጨረታ ዋጋ ላይ በመንተራስ በፐርሰንት አሳንሶ ወይም አስበልጦ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ካወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናቶች ዘወትር በሥራ ሰአት ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ኮምቦልቻ ዋና መ/ቤት ገንዘብ ቤት እና አዳማ ቅ/ፍ ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛታ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው የጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት አዳማ ቅ/ፍ ጽ/ቤት፣ አዲስ አበባ ማስ/ጽ/ቤት እና ኮምቦልቻ ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው መዝጊያ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 በሥራ ሰአት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮምቦልቻ ዋናው መ/ቤት፣ አዲስ አበባ ማስ/ጽ/ቤት እና አዳማ ቅ/ፍ ይከፈታል ነገር ግን 16ተኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተቀመጠው ሰዓት ላይ የሚከፈት እና የሚዘጋጠ ይሆናል።
7. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ካሸነፋበት ቀን ጀምሮ በ8 /ስምንት/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፣ በስምንት ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ማድረግ ካልቻሉ አሸናፊነታቸው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም።
8. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን በ10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
9. በጨረታው ለተሸነፉት ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
10. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ የስልክ ቁጥር ኮምቦልቻ 033 551 4219 አዳማ 022 112 6241 አዲስ አበባ 011 557 5115
ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎ/ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-11-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-07 10:30
- Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tikur Abay Transport Private Limited Company
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
- Posted at: 2026-10-23T08:24:31.000Z
- Source: Qelal Tenders